አዝ፦ እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ እልፍ ወደ ማዶ አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ ሊያሳየኝ አቅዶ ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ ሁሉ እንዲደነቁ ከልምምድ ውጪ ከተዘወተረው አዲስ ነገር መስራት ልማዱ የሆነው በውኃ ላይ እንድሄድ እንድቆም አዘዘኝ . (1) . እና አትፍሪ ነይ አለኝ ውኃ ላይ በታንኳ ሁሌ ከመንሳፈፍ ኢሄም አለ ብሎ አደረገኝ እልፍ ከታንኳ ለወረዱ ቢሉም ምትሃት ነው ለካስ የእኔ ጌታ ውኃም መንገዱ ነው አዝ፦ እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ እልፍ ወደ ማዶ አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ ሊያሳየኝ አቅዶ ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ ሁሉ እንዲደነቁ እንሂድ ወዲያማዶ እንሂድ እንሻገር ሥሙም ጌርጌስ ሄኖን ወደሚባል አገር ለረጅም ዘመናት ብዙ የተቸገረ በመቃብር ስፍራ አለና የታሰረ እልፍ እንበልና የታሰረ ይፈታል ብሎ ሲያሻግረን ይሄ ቸሩ ጌታ በስፍራው ስንደርስ ይህ ሰው ተፈወሰ ጌታም ተገናኘው ህማም ተመለሰ አዝ፦ እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ እልፍ ወደ ማዶ አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ ሊያሳየኝ አቅዶ ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ ሁሉ እንዲደነቁ ሌሊቱን በሙሉ ስደክም ፍለጋ መረቤም አንድ ዓሣ ሳይዝልኝ ነጋ የጌታን ቃል ይዤ ስጥል ወደ ጥልቁ ታንኳዬን ዓሣዎች ሞልተው አስጨነቁ መሄድ እንደቃሉ ፈቀቅ ማለት በውስጡ አለና ብዙ በረከት ገፍቶ አስጠግቶኝ አድርጐኝ እልፍ በመንፈሱ ሙላት ሆነ መንሳፈፍ አዝ፦ እልፍ ወደ መሃል እልፍ ወደ ማዶ አሃሃ እልፍ ወደ ማዶ አረገኝ ማዳኑ ሊያሳየኝ አቅዶ ኦሆሆ ሊያሳየኝ አቅዶ ፈቀቅ ወደ መሃል ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሃሃ ፈቀቅ ወደ ጥልቁ አሰራሩን ያዩ ሁሉ እንዲደነቁ ኦሆሆ ሁሉ እንዲደነቁ