የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል የጌታ ሥራ እጅጉን በዝቷል ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ ነግሮ ሊጨርስ ማነው የቻለ ተዓምራቶቹን እያስተዋለ የጌታን ክብር ታላቅነቱን የፍቅሩን ብዛት ደግሞ ጥልቀቱን ከመጣው በቀር ሁሉ ያለፈ ከህሊናችን ሞልቶ የተረፈ ነውና ታላቅ ሥራው ብዙ ለዚህ ለጌታ ምሥጋናውን አብዙ ይሄ ሁሉ ፍጥረት የሚያመሰግንህ ይሄ ሁሉ ክብር ለአንተ የተገባ ስለሆንክ ገዢ ብርቱና ገናና አሁንም አሁንም ይብዛልህ ምሥጋና ፍጥረታት በሙሉ በግዛትህ ናቸው ስለዚህም በአንተ ብዙ ደስታ አላቸው በራሳቸው ቋንቋ ይመሰክራሉ የእግዚአብሔር ሥራ ፍጥረት ነን እያሉ ሃሌሉያ የለህም መሳይ (3x) በምድር በሰማይ የለህም እኩያ (3x) ኦ ሃሌሉያ በደማቅ ብርሃን እራስክን ሰውረህ ከፍ ካሉት በላይ እጅግ ከፍ ብለህ ድካምና ዝለት ሳያውቅህ እርጅና ትናንትና ዛሬም ሁልጊዜ ገናና ንጉሥ በንግሥናው አዋቂው በዕውቀቱ ሊመስልህ ሲሞክር ሲጥር አይ ሰው ከንቱ ነገር ግን ከአንተ ጋር ሁሉን ሲያስተያይ ሁሉን ብሎ ያልፋል የለህም መሳይ ሃሌሉያ የለህም መሳይ (3x) በምድር በሰማይ የለህም እኩያ (3x) ኦ ሃሌሉያ እግዚአብሔር እንዲህ ይህን ይመስላል ተብሎ በቃላት መች ይገለጻል አንዲያ ልጁ በቀኙ ያለው ተረከው እንጂ ሌላ ማን አየው ሰማይ ተቀምጦ እግሮቹ ምድር ታላቅነቱ እንዴት ይነገር መግለጫ ቋንቋ ቢጠፋም ቃሉ እንዲሁ ብቻ ተመሥገን በሉ የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል የጌታ ዝና እጅጉን በዝቷል ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ የለህም መሳይ (3x) በምድር በሰማይ የለህም እኩያ (3x) ኦ ሃሌሉያ (2x)