Song Lyrics

አሸናፊ ነኝ

Azeb Hailu
Ashenafi Negn
እንደ ጀግና ወንድ/ሰው እንደ እልፍ ገዳይ እንጐራደዳለሁ/ፎክርበታለሁ በጠላቴ ላይ ተረታው ሳይል እጁን ዘርግቶ ማጥቃት መዋጋትን አልተውም ከቶ (2x) ተወርውሮ ከቶ የማይስተው የጌታዬ የኢየሱስ ሥም ነው ደጋግሜ እርሱን ጠራዋለሁ በጠላቴ ላይ ከፍ እላለሁ ሲቀረቀር በግንባሩ ላይ በእጄ ያለው የያዝኩት ድንጋይ ላዩ ቆሜ አንገቱን ቆርጥና አውጃለሁ የጌታዬን ዝና አዝ፦ አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (2x) እኔም እንደ ዳዊት እንደ እግዚአብሔር ሰው በሕዝቤ ጠላት ላይ ሥምህን ላንሳው በሰልፉ ሜዳ ላይ ወደ መሃል ልግባ ጠላትን ዘርሬ ላፍስስ የደስታ እንባ እኔ እያየሁ በጐልያድ በእሰይ ላይ አይፎክርም እኔ እያለሁ ጠላት በሕዝቤ/በምድሬ ላይ አይዘብትም (2x) የአንበሳን ደቦል የሚገነጥል ግዙፉን ሠራዊት ሰባብሮ የሚጥል የአምላኬ ክብሩ ነው ከእኔ ጋራ ከቶ እንደምን ልስጋ እንዴትስ ልፍራ (2x) ፍልስጤሞች ያገኙኝ መስሏቸው በመንደሩ ሞላ ዕልልታቸው መጠንቃረው ገመድ አስረውኛለው በእነሱ ቤት ማን ያስጥለኛል ወረደብኝ መንፈሱ የጌታ እስራቴም ላላ ተፈታታ በእጄ ገቡ ጠፉ ጠላቶቼ ገመድኳቸው መጥቼ ፈትቼ አዝ፦ አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (2x) አሞት ይሆናል ወይ መንገድ ሄዶ አንቀላፍቶም ይሁን ይህ ከንቱ ባዶ በአሕዛብ አምላክ እሳለቃለሁ በማንነቱም ላይ እዘብታለሁ (2x) አምላክ ሳይሆን አምላክ ነኝ ባዩን መዘዝኩበት ስለታም ሰይፌን ነብያቱን በሙሉ አረድኳቸው እስቲ ያድን ይምጣ አምላካቸው የሚመልስ በእሳት ተገልጦ የአሕዛብን አምላክ አስደንግጦ የእኔ ጌታ ሥሙም እግዚአብሔር ከፍ ብሎ ተከብሮ የሚኖር አዝ፦ አሸናፊ ነኝ የጌታ/የኢየሱስ ሆኜ አፍሬ አላውቅም እርሱን ታምኜ (2x) እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ኤልያስ በምድር ኢትዮጵያ ላይ ሥምህ እንዲነግስ ከበዓል ነብያት እወራረዳለሁ ክብርህን ስትገልጥ እረታቸዋለሁ እኔ እያየሁ በአል አምላክ ተብሎ አይመለክም እኔ እያለሁ የጌታዬ/የኢየሱስ ክብር አይሸፈንም (2x) አንተ እያለህ እውነት እንጂ ውሸት አይሰበክም አንተ እያለህ ወንጌል እንጂ ክደት አይነገርም አንቺ እያለሽ እውነት እንጂ ውሸት አይሰበክም አንቺ እያለሽ ወንጌል እንጂ ክደት አይነገርም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection