Song Lyrics

ከፍ በል

Aster Yosef
Antew Tishalegnaleh
አዝ፦ ከፍ በል (4x) በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል ከፍ ካለው በላይ ከፍ ላልከው ለአንተ ምሥጋናን እሰጣለሁ (2x) ሥምህን ጠርቼ አላፈርኩምና ድንቅህ ለሕይወቴ ብዙ ነውና ፊትህ ወድቄ ላቅርብ ምሥጋናዬን ከፍ ከፍ ላርግህ ባለውለታዬ ከፍ በል (4x) በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል ከፍ ካለው በላይ ከፍ ላልከው ለአንተ ምሥጋናን እሰጣለሁ (2x) ጠላት ሊይዘኝ ከኋላዬ መጥቶ ባህሩም ሲናወጥ እስከ አፉ ሞልቶ በዘረጋሁ ጊዜ በትሬን በእምነት በድል ተሻገርኩ ሰጠመ ጠላት አምላኬ ነህ አምላኬ (6x) አይቻለሁ ማዳንህን አይቻለሁ ጥበቃህን አይቻለሁ ችሎታህን አይቻለሁ ብርታትህን አይቻለሁ ምህረትህን አይቻለሁ ያን ፍቅርህን አይቻለሁ ጉልበትህን አይቻለሁ ስልጣንህን እንደ እግዚአብሔር ያለ ኧረ ማን አለ (2x) እንደ ኢየሱስ ያለ እስኪ ማን አየ (2x) ይናገር ማን አየ ኧረ ማን አየ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም እንደ ኢየሱስ ያለ ማንም የለም (2x) አንተን ማን ይመስላል በዘመናት መሃል ከአንተስ ጋር እግዚአብሔር ማን ይወዳደራል የነገሥታት ንጉሥ የኃይላን ኃያል ገናናው እግዚአብሔር አንተን ማን ይመስላል እንደ አንተ ያለ የለም (2x) እንደ አንተ ያለ የለም ለዘለዓለም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection