እነዚያስ ያንን የተማመኑበት ተሰነካከለ ተስፋ ያደረጉበት ክብራቸው ወደቀ ቀንዳቸው ተመታ በዙፋኑ ከብሮ አለየእኛ ጌታ ብቻህን ተዐምራት ያደረግህ ጌታ ፍፁም የማትረታ አዝ፦ በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ ሠማይን እንደ መጋረጃ ዘርግቶ እልፍኙን በውኃ አሳምሮ ሰርቶ ምንም የሌለበት እጅግ ከደረቀ አለቱን ሰንጥቆ ውሃን አፈለቀ (2x) አዝ፦ በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ ሸለቆን የሚሞላ ተራራን የሚንድ አገልጋዩን እንደ ነበልባል የሚያነድ በተራሮች ላይ ውሆችን የሚያቆም እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ የለም አዝ፦ በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ በሚንበለበለው እሳት ውስጥ ቢከተን የምታምኑት አምላክ ያድናችሁ ቢለን የምናምነው አምላክ ዝም ብሎ አያየን ነጥቆ ያወጣናል ከእሳቱ ወላፈን (2x) አዝ፦ በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ መዝገቡም ይከፈት ታሪክም ይመርመር አንደበትም ያውራ መስካሪም ይመስክር ብርቱ የሆነ አምላክ ማነው ከአንተ በቀር የሚነደውን እሳት በእሳት የሚሽር (2x) አዝ፦ በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ