Song Lyrics

ተመሥገን

Aster Yosef
Antew Tishalegnaleh
ተመሥገን (10x) ከአብ ዘንድ ያለኸኝ ለእኔ ጠበቃዬ በፍቅር የምታየኝ ወዳጅ አፍቃሪዬ ፈልጌ የማላጣህ የምትቆም ከጐኔ አንተ ነህ ኢየሱስ ድጋፍ መከታዬ (2x) ልዩ ወዳጄ ነህ ቋሚ ተጠሪዬ ለሚደርስብኝም ነህ ተቆርቋሪዬ ከእኔ የማትለይ የማትጠፋ ከጐኔ አንተ ነህ ኢየሱስ ተሟጋች ለነፍሴ (2x) ተመሥገን (10x) ከገመትኩት በላይ ፍቅሩ ለእኔ በዛ ፍፁም አይገመት እንዲህ እንደ ዋዛ ግርዶሼን ቀደደው ልጁን አድርጐ ቤዛ እግዚአብሔር ወደደኝ በፍቅሩ እኔን ገዛ (2x) ፍቅሩ እጅግ ግሩም ነው ከሁሉም የሚስብ ያየ የሰማውን እጅግ የሚያስደንቅ በከበረው ዙፋን ነፍሴን አኖረልኝ ሁሉንም ድል አድርጐ ድል አወጀልኝ (2x) ተመሥገን (10x) መላእክት ተደፍተው ለሚሰግዱልህ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ለሚያዜሙልህ እኔም ተነስቼ ቅዱስ ነህ እላለሁ ከእግርህ ሥር ወድቄ ክብርን እሰጣለሁ (2x) በዕልልታ ሽብሸባ ቤትህ እገባለሁ ሁሌም አምላኬ ነህ እገዛልሃለሁ ለአንተ የሚሳንህ አላየሁምና ዛሬም እልሃለሁ ይብዛልህ ምሥጋና ዛሬም ነገም ለአንተ ይብዛልህ ምሥጋና (2x) ተመሥገን (10x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection