Song Lyrics

ምን ይሳንሃል

Aster Yosef
Antew Tishalegnaleh
አዝ፦ ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (2x) የእስራኤልን ሕዝብ ከባርነት ምድር በውኑ ሊያወጣ ሙሴ ማን ነበር አፌን በአፍህ ላይ አደርጋለሁ ብለህ ላክኸው ወደ ፈርዖን ኮልታፋውን መርጠህ በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ ይህን ታደርጋለህ (2x) አዝ፦ ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (2x) ብዙ የተማሩ አዋቂዎችን ትተህ ዓሣ አጥማጆችን ለራስህ መረጥህ እጅግ ታናናሾች ተራ በተባሉት ዓለምን አዳረስክ በወንጌልህ እሳት በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ ይህን ታደርጋለህ (2x) አዝ፦ ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (2x) ልባቸው ሲቀልጥ በዮርዳኖስ ሙላት ታቦት ተሸክሙ እነዚያ ካህናት በተንጣለለው ወንዝ ሰገባ እግራቸው ለሁለት ከፍለህ አንተ አሻገርካቸው በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ ይህን ታደርጋለህ (2x) አዝ፦ ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (2x) ለመሞት ጥቂት ቀን የቀራትን አይተህ እንድትመግበው ደሃዪቱን አዘህ ከኮራት ፈፋ ውስጥ ጌታ አውጥተኸው በሰራፍታ ምድር ኤሊያስን መገብኸው በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ ይህን ታደርጋለህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection