የትኛው ወዳጅ ነው የትኛው አባት እስከ ዛሬ ድረስ ሳይደክም ሳይታክት ሊሸከም የሚወድ ከኃጥያት ከነክፋቴ ጌታ አንተን ብቻ አየሁ ፍፁም አፍቃሪዬ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (4x) ይገርማል መወደዴ ይገርማል መፈለጌ ይገርማል መመረጤ ይገርማልመፈጠሬ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (4x) ንጉሥ አዋጅ ቢያውጅ ጠላቴ ተጣድፎ እርግማን ሊረግመኝ ባላቅም ተቻኩሎ በለአም ግን ትእዛዝ ከላይ ተቀበለ አዋጅ ሻረ ጌታ ታሪክ ተለወጠ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (2x) ደነቀኝ ደነቀኝ ደነቀኝ (2x) ይገርማል መታሰቤ በዓይኖቹ መታየቴ ገረመኝ እኔ መትረፌ በእጆቹ መያዜ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (3x) የመኖሬን ሚስጢር ሳስብ ይደንቀኛል ዛሬ ላይ መቆሜ እጅግ ይገርመኛል አንተ ከላይ ሆነህ በዓይኖችህ አየኸኝ ምህረት ማፅናናትህ እጅግ ደስ አሰኘኝ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (2x) ደነቀኝ ደነቀኝ ደነቀኝ (2x) ይገርማል መወደዴ ይገርማል መፈለጌ ይገርማል መፈቀሬ ይገርማል መመረጤ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ ደነቀኝ ደነቀኝ ደነቀኝ (2x) ማንም ያልራራልኝ መንገድ የተጣልኩኝ በደም ተነክሬ ሞቴን የጠበቅሁኝ በእጅህ ታክሜ ድኜ ከህመሜ ከመሞት አምልጬ ገረመኝ መቆሜ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (4x) ይገርማል ኧረ መትረፌ ከክፉዎች ማምለጤ ገረመኝ አሰራርህ ፍጥነትህ አደራረስህ ገረመኝ ገረመኝ ገረመኝ (3x)