Song Lyrics

አንተው ትሻለኛለህ

Aster Yosef
Antew Tishalegnaleh
የንጉሥ ልጅነት እንቢ ያለ ግብፅንም በእምነት የተወ ሳያየው እንደሚያየው ቆጥሮ ብድራቱን አይቶ አሻግሮ ምንም እንኳን የግብፅን ጥበብን ቢማርም ሙሴ የባእድ ዕውቀት ከቶ አልማረከውም ከገንዘብም ይልቅ መከራን መረጠ ስለ ሥምህ ለአንተ መነቀፍን ወደደ አዝ፦ ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ አለውጥም የነፍሴን ጌታ ብድራቴን ልየው አሻግሬ የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ አንተ ትሻለኛለህ (8x) አንተ ታዋጣኛለህ (8x) በቁጥቋጦው መሃል ታየኸው እግዚአብሔር አምላኩ ቀረብከው ሾምክና ወደ ሕዝብህ ላክኸው በሞገስ ወጣህና አብረኸው በብርታትህ ጉልበት የበረታ ሆነ በድፍረት ንጉሥ ፊት ለመቆም ታመነ የሰጠኸውን በትር በእምነት ይዞ ወጣ እስራኤልን ከግብፅ ባርነት አወጣ አዝ፦ ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ አለውጥም የነፍሴን ጌታ ብድራቴን ልየው አሻግሬ የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ አንተ ትሻለኛለህ (8x) አንተ ታዋጣኛለህ (8x) ትሁት ሆኖ ተመላለሰ በህዝቡ መቃወም ታገሰ እንዳለው ወደ አንተ ማለደ ጥፋቱን ማየት መች ወደደ ብድራቱን አይቶ ለዓላማው ጨክኖ የንጉሥ ልጅ ሲባል በእምነት እንቢ ብሎ ሳይፈራና ሳይደነግጥ የንጉሡን ቁጣ በትሩን አነሳ ጠላትን ድል ነሳ አዝ፦ ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ አለውጥም የነፍሴን ጌታ ብድራቴን ልየው አሻግሬ የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ አንተ ትሻለኛለህ (8x) አንተ ታዋጣኛለህ (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection