አዝ፦ አቻና ተወዳዳሪ የለህም ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (3x) እንዴት እንዳቆምካት ምድርና መሰረቷን በምን እንዳፀናሃት የድንጋይ ማእዘኗን ብቻህን ጌታ ነህ (4x) የባሕር ዳር ድንበሩን ለአንተ ማን አሳየህ ሁሉ በቃልህ ሆነ ሰምቶህ እየታዘዘህ (2x) አዝ፦ አቻና ተወዳዳሪ የለህም ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (3x) ከአህዛብ ጥበበኞች የሚመስልህ ማን አለ ከመንግሥታቸውም ውስጥ ተወዳዳሪ የለህ ብቻህን ጌታ ነህ (4x) ሁሉም ፍጥረት በፊትህ ለአንተ ይንበረከካሉ ወደዱም ጠሉም ለክብርህ ወድቀው ይሰግዳሉ (2x) አዝ፦ አቻና ተወዳዳሪ የለህም ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (3x) ይሄ የሰማነው ምንኛ እጅግ ጥቂት ነው የኃይሉንስ ነጐድጓድ የሚያስተውለው ማነው ብቻውን ጌታ እኮ ነው (4x) ትልቅ ነው እርሱ እግዚአብሔር ሃሳቡን የሚያውቅ ማነው በሠማይም በምድር እኩያ አቻ የሌለው (2x) አዝ፦ አቻና ተወዳዳሪ የለህም ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (3x) ብቻህን ጌታ ነህ (4x)