ያመንኩትን አውቃለሁ የተረዳሁትን አንዱም አይጣል ከእርሱ የሰማሁት በእጄ እንዳለ እንደጨበትኩት ያህል ነው የምቆጥረው እንደያዝኩት (2x) አምላኬ አምላኬ እርሱ ይታመናል ከተናገረው የቱንስ አስቀርቷል አምላኬ አምላኬ እጅግ ይታመናል ካለበት ቀን እልት መቼ ፈቀቅ ብሏል (2x) እለት እለት እርሱን ሳወጣና ሳወርደዉ ቃሉን በአፌ አኑሬ እርሱን ብቻ ሳመላልሰዉ ጥቅልሉን ስፈታ ውሉን ይዤ ስተረትረዉ በዓይን ያልታየው ይገለጣል ጆሮ ያልሰማው (2x) ቃል ከአፉ ሲወጣ አልጠራጠረዉም በልቤ አኑሬ እምጠባበቀዉም ፈጽሞ አይሆንልኝ ችላ ችላ ማለት እይዘለለ ውስጤ መች ይሰጠኝ እረፍት (2x) አምላኬ አምላኬ እርሱ ይታመናል ከተናገረው የቱንስ አስቀርቷል አምላኬ አምላኬ እጅግ ይታመናል ካለበት ቀን እልት መቼ ፈቀቅ ብሏል (2x) ጌታዬ ብዬ አመልክሃለሁ ወዳጄ ብዬ አመልክሃለሁ (2x)