መተማመኛዬ የተማመንኩበት አያሳፍረኝ የተደገፍኩት በፍፁም አልሰጋ ግራም አይገባኝ ሊያደርግ ያለውን ከእኔ አይሰውረኝ (2x) የእኔ ጌታ የታመነዉ ቃሉን በሥራ የገለጠዉ የእኔ ኢየሱስ የታመነዉ በስጦታው አይጸጽተዉ (2x) ታማኝነቱ አጥብቆ ያዘኝ መቼም ከእጆቹ እኔን ላይለቀኝ በእኔ መጨከን አይሆንለት ምህረቱ ብዙ የእሱስ አያልቅም ልበለው እንጂ ተባረክ (3x) አትለወጥም ተባረክ (3x) አንተ ታማኝ ነህ ተባረክ (3x) ተባረክ ጌታ ተባረክ ተባረክ ሁሌ/ዘለዓለም ተባረክ (2x) በጌታ ተማምኖ ከመንገድ የቀረ ማን አንገቱን የደፋ ማን ያቀረቀረ አታፍሪም እንዳለ መቼ ያሳፍራል ከመቅደሱ ሆኖ ድሉን ያፈጥነዋል (2x) የእኔ ጌታ የታመነዉ ቃሉን በሥራ የገለጠዉ የእኔ ኢየሱስ የታመነዉ በስጦታው አይጸጽተዉ (2x) ታማኝነቱ አጥብቆ ያዘኝ መቼም ከእጆቹ እኔን ላይለቀኝ በእኔ መጨከን አይሆንለት ምህረቱ ብዙ የእሱስ አያልቅም ልበለው እንጂ ተባረክ (3x) አትለወጥም ተባረክ (3x) አንተ ታማኝ ነህ ተባረክ (3x) ተባረክ ጌታ ተባረክ ተባረክ ሁሌ/ዘለዓለም ተባረክ (5x)