Song Lyrics

እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ

Aster Moges
Ene Aliwerdim
እልፍ እያለ የሚሄድ የኋላውን ጥሎ የጌታውን ፍለጋ ዱካውን ተከትሎ አስቀድሞ ይወጣል ልቡን እያስደፈረ አስተውሎ ያደርጋል ዘመን እየመረመረ (2x) እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ እንደ ኃያል በጠላቶቼ ላይ ወረደ እያንዳንዱን ሊበቀል (2x) ጠጠር ይዞ የማይፈራ አሃሃ የጠላቶቹ ዛቻና ፉከራ እህህ (2x) ከአምላኩ የተማረው የሰማ ነው ያሸነፈው (4x) ህዝቡን ያሸበረው እስኪ የቱ ነው ብሎ ከሰልፉ መሃል ይወጣል በአምላኩ ተማምሎ ዋነኛውን ሳይጥለው እርሱ አያፈገፍግም ጭፍራውን ሳይበትነው ደግሞ አይመለስም (2x) እግዚአብሔር እንደ ጨካኝ እንደ ኃያል በጠላቶቼ ላይ ወረደ እያንዳንዱን ሊበቀል (2x) ጠጠር ይዞ የማይፈራ አሃሃ የጠላቶቹ ዛቻና ፉከራ እህህ (2x) ከአምላኩ የተማረው የሰማ ነው ያሸነፈው (4x) ይሄስ የማነው ጀግና የማነው እርሱ ይሄስ የማነው ጐበዝ የማነው እርሱ (2x) አሳየው እንጂ ቆርጠህ እራሱን አሳየው እንጂ ቆርጠህ አንገቱን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection