Song Lyrics

ገና ከመጀመሪያው

Aster Moges
Ene Aliwerdim
ገና ከመጀመሪያው ከዚያን ቀን ጀምሮ አሁንም ሊሰራኝ እጅግ አሳምሮ ፈቀቅ አደረገኝ እኔን ወደ ማዶ ከፊት ይልቅ ሊያሳየኝ ሊያበራልኝ ወዶ አዝ፦ ሁሉ በሁሉ ነው ሁሉን ነገር ያውቃል አምላኬ ስለእኔ አጅግ ግድ ይለዋል በፍፁም አይደክም አይታክት ስለእኔ በአንዳች አንዳልጐድል አይለይ ከእኔ ድካሜን አይወድም ክብሬን ይናፍቃል ሁሉን ስለሰጠኝ ሊያየኝ ይፈልጋል ካሰበልኝ በታች እንደኖር አይፈቅድም እርሱን ደስ የሚለው ያይልኝን ስፈጸም ነው አዝ፦ ሁሉ በሁሉ ነው ሁሉን ነገር ያውቃል አምላኬ ስለእኔ አጅግ ግድ ይለዋል በፍፁም አይደክም አይታክት ስለእኔ በአንዳች አንዳልጐድል አይለይ ከእኔ እንደ ንጋት ብርሃን ክብሩ እይጨመረ ከክብር ወደ ክብሩ እያሸጋገረ በከፍታዎቹ ላይ እንድራመድ ዘወትር ይመራኛል ከፍ ከፍ እንድልለት አዝ፦ ሁሉ በሁሉ ነው ሁሉን ነገር ያውቃል አምላኬ ስለእኔ አጅግ ግድ ይለዋል በፍፁም አይደክም አይታክት ስለእኔ በአንዳች አንዳልጐድል አይለይ ከእኔ ጌታዬ ነዉ (ጌታዬ) አምላኬ ነዉ ጌታዬ ነዉ (ጌታዬ) አምላኬ ነዉ (አምላኬ ነው) ለእኔ የሚራራዉ እኔን የሚረዳዉ (2x) እርሱ ብቻ ነው ለእኔ የሚራራዉ እኔን የሚረዳዉ (2x) እርሱ ብቻ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection