ረድኤቴ እግዚአብሔር ሆይ ዛሬም ከእኔ ጋር አለህ ጉዳይ የጀመርከውን ሳትጨርሰዉ አታርፍምና ሳትፈጽመዉ (2x) ልቤን አሰፋህ ውስጤን አሰፋህ ዙሪያዬን አሰፋህ አንተ ስትመጣ (2x) እጀህ ተዘርግቷል ማን ሊመልሰው በረከትን ከላይ ሊያዠቅዢቀው (4x) ብቻህን ክበር አንተው ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ በክብር ተመላለስ (2x) አንተ ማንንም ጌታ የማትረሳ ሁሉም በጊዜው አንተ የምታነሳ የተናገርከውን አታዘገየው እጅ በእጅ ውዲያው ሳታወራርደው (2x) ፊትህ አበራ ሞገስህ አበራ ክብርህ አበራ አንተን ስጣራ (2x) ድጆች ተከፈቱ ተነቀለ መዝጊያው በቃ ተሰበረ የብረት መወርወሪያው (4x) ብቻህን ክበር አንተው ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ በኃይል/በክብር ተመላለስ (2x) ተመላለስ በኃይልህ ተመላለስ በክብርህ (4x)