ይገባሃል መሰጠቴ አክብሮቴ መገዛቴ ይገባሃል ማንነቴ ይህ ህይወቴ እራስህን ለኔ ሰጠህ ቅድስና ባህሪህ ነው (ኔም ላንተ ሆ) እኔም ላንተ እቀደሳለሁ እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ አባት እያልኩህ ክብር አልነፍግህም ጌታ እያልኩህ አላዋርድህም በከንፈር ብቻ አለሁ እያልኩኝ በራቀህ ልቤ አላመልክህም እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ አባት ነህና ያባትነትክን መገዛት ጌታ ነህና የሚገባህን መፈራት እሰጥሃለሁ አመልክሃለሁ ከፍፁም ልቤ ያንተ መክበር ነው ጥማት ረሃቤ እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ ላመልክህ እወዳለሁ ክብሬን ልጥልልህ አንተን ማመስገኔ ክብር ነው ለእኔ እገዛልሃለሁ /4/ ሁሌ አመልክሃለሁ