ጨለማው ተገፏል ፅልመት ተወግዷል ፍርሃት ጭንቀት ሄዷል ጌታ ደርሶልናል በሞት ጥላ ላለን ብርሃን በርቶልናል ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ሆኖልናል የሞት መውጊያው መሳሪያው ተሰበረ መንደፊያው የዲያብሎስን ስራ ሊያፈርስ ተገለጠ ጌታ ኢየሱስ የሃጢያትን ጉልበት ሊያፈርስ ተገለጠ ጌታ ኢየሱስ የሞት ሽታ የሞት ጠረን ትናንትና ከቦን ነበር ዛሬ ብርሃን በርቶልናል የ እግዚአብሔር ልጅ ደርሶልናል የእሳቱ ኃይል ጥንካሬው እጅግ ቢከብድ ቢደርስ ሰማይ ልጁን ልኮ አውጥቶናል ከሳቱ ሃይል አድኖናል