ቢልቃጡ ተሰብሮ ሽቶው ያውድህ ነፍሴም ትገዛልህ እምባዬም ይፍሰስ እኔ ዝቅ ልበል አንተን ከፍ ላርግህ ክብሬን ልጣልና ክብርህን ላምጣልህ ክበርልኝ ያጢያተኛው ወዳጅ ነህ ሰው የራቀውን ምትጠጋ የልቡን በር ዘልቀህ ገብተህ ጨለማውን ምታነጋ መድኃኒት ሆንካት ለነፍሴ እስራቴን ፈታህና በማዕድህ አስቀመጥከኝ እኔም ባንተ ታሰብኩና የኔ መዝሙር የኔ ዜማ የኔ ልቅሶ የኔ እምባ ምስጋናን ቢጨምር እንጂ አንተስ ከጥንት የተቀባህ ንግግሬ ብቻ አይደለም እርምጃዬም ያስደስትህ እኔ ያለ ልክ ዝቅ ልበል አንተ ያለ ልክ ከፍ በል ገና ከጥንት ስትመራኝ ስትመክረኝ አውቅሃለሁ ዛሬ ቤቴ ልትገባ ተራ ደርሶኝ ታስቤያለሁ ሳልወድህ እየወደድከኝ አኔ ታዲያ ምን እላለሁ ቤቴ ባንተ ካማረልኝ ነፍሴን ፊትህ አፈሳለሁ