Song Lyrics

ፈውሴ ለነፍሴ

Asrat Mulachew
Hiwotih Hiwote
ፈውሴ ለነፍሴ በመመለሴ እንደሆነ አውቄያለሁ መልሰኝ እመለሳለሁ መልሰኝ መልሰኝ መልሰኝ እመለሳለሁ ፈውሰኝ ፈውሰኝ ፈውሰኝ ድኜ ቀራለሁ እርኩሰት አብዝተን በደል ጨምረናል አመጽን በመዝሙር በጩኸት ከድነናል ማረን ይቅር በለን ተመለሱ የሚል ምክርህን ንቀናል ልዑሉ በሰማይ መኖርህን ረስተናል ማረን ይቅር በለን አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን አቤቱ ፈውሰን እንፈወሳለን አቤቱ አድነን እኛም እንድናለን አቤቱ መልሰን እንመለሰላን ኦ ማረን ማረን ይቅር በለን /4/ ጥላቻና ትዕቢት ንቀት አስክሮናል ይቅር ማለት ከብዶን ከምህረት ጎድለና ማረን ይቅር በለን ፍሬ ሳናፈራ እንባ ማብዛታችን ከቶ አልጠቀመንም ግብዝነታችን ማረን ይቅር በለን ጎራ እየለየን ውጊያ ሰልጥነናል ክቡር ደምህን ረግጠን ወንድምን ገድለናል ማረን ይቅር በለን የሰጠኸን ገንዘብ ጌታ ሆኖብናል በኢየሱስ ስም እያልን ነፍስን አሳደናል ማረን ይቅር በለን ማጉረምረምን ትተን ስለቅጣታችን ወዳንተ እንመለስ ይቅር መንገዳችን ማረን ይቅር በለን ወደላይ ይነሳ ልባችን ከእጃችን ደመናትን ይለፍ ይሂድ ልመናችን ማረን ይቅር በለን መሪር ሃዘን ሊሆን ኢካቦድ ተወልዶ ካንተ ፊት ሲጠፋ ሰው ሃጢያት ተላምዶ ማረን ይቅር በለን እያየን ሲርቀን ክብርህ ከፊታችን ዛሬ ላይ መልሰን አንተው ነህ ተስፋችን ማረን ይቅር በለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection