መቼም ብዙ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ በባህሪያቸው አማልክት ሳይሆኑ አምላክ ነን የሚሉ ከማንም/ከየቱም ጋር ሳታነፃፅርህ ሳታወዳድርህ ነፍሴ ወዳህ በላይዋ ሾመችህ አንተን እግዚአብሔር የነፍሴ ምርጫ ነህ የነፍሴ /2 የቤቴ ምርጫ ነህ የቤቴ/2 መቼም ኑሮ አይሞላ ቢለፋ ቢደከም አንተ የሌለህበት ሩጫ ዋጋ የለውም/ሩጫም አያረካም ፅድቅህን የፈለገ መንግስትህን ያለ እርሱ ነው በሰማይ በምድር የታደለ የነገሮች መሙላት የነገሮች መጉደል ለመስፈርት አይቀርብም አንተን ለመከተል ከብዙ ዕልፍ መሃል የተመረጥክ ነህ ልክ እንደአባቶቼ ለኔም ምርጫዬ ነህ የሁሉ ጌታ ነህ ምርጫዬ ያረኩህ ያዋጣኛል ብዬ የተከተልኩህ ለሰማዩ ቤቴ ዋስትና ከሆንከኝ እኔ ለምን ልፍራ በምድር እያለሁኝ ምርጫዬ ነህ /2/ እኔና ቤቴ ምናመልክህ ምርጫዬ ነህ /2/ በኔና በቤቴ የምትመለክ