Song Lyrics

ዘላለም አመልክሃለሁ

Asrat Mulachew
Hiwotih Hiwote
አንት ከከበርክ እኔ ምን እሻለሁ ያንተ መክበር ያ የኔ ደስታ ነው ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ ድምፅህን ስሰማው እጅግ ደስ ይለኛል ሽር ጉድ ስልልህ ክብር ይሰማኛል ረሃቤም ጥማቴም ፈቃድህን ማድረግ ነው ፃድቁን አይቼ ጠግቤ መኖር ነው ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ ሙሽራው ሲከብር ደስ እንዲለው ሚዜ ደስታዬ ይሞላል ከብረህ ሳይህ ጊዜ ድመቅ በሁሉ ላይ ታይልኝ ቀን ሙሉ ፍጥረታት ሁሉ አይተው ጌታዬ ይበሉ ክብር ይሁን በላይ ክብር ይሁን በሰማይ በፍጥረት ሁሉ ላይ አንተ ብቻህን ታይ ክብር ይሁን በታች ክብር ይሁን በምድር በእጆች ስራ ላይ አንተ ብቻ ክበር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection