ይችላል /4/ ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ለሰው የማይቻል ለ እግዚአብሔር ይቻላል ሃኪም ያቃተውን ደዌ ይፈውሳል እግዚአብሔር ይችላል ህዝብን ያናወጠን ማዕበል ይገስፃል እግዚአብሔር ይችላል እርኩስ መንፈስ ፊቱ መች ችሎ ይቆማል እግዚአብሔር ይችላል ለኢየሱስ ክብር ወድቆ ይንበረከካል እግዚአብሔር ይችላል ይችላል /2/ እግዚአብሔር ይችላል ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ለሰው የማይቻል ለ እግዚአብሔር ይቻላል ነፋስን ይጠራል ባህር ዝም ያሰኛል እግዚአብሔር ይችላል የተፍገመገመን አፅንቶ ያቆማል እግዚአብሔር ይችላል አለትን ሰንጥቆ ጥማትን ያረካል እግዚአብሔር ይችላል ጥቂት ባርኮ አብልቶ ሺሁን ያበረታል እግዚአብሔር ይችላል ተራራውን ንዶ ደልዳላ ያደርጋል እግዚአብሔር ይችላል ደረቁን ሸለቆ በውሃ ይሞላል እግዚአብሔር ይችላል መንፈሱን ያፈሳል ህይወትን ያድሳል እግዚአብሔር ይችላል ሳይታክት ለሚጮህ እግዚአብሔር ይመጣል እግዚአብሔር ይችላል ዕውርን ያበራል ሽባን ያዘልላል እግዚአብሔር ይችላል እንቆቅልሽ ፈቶ ቋጠሮ ይበጥሳል እግዚአብሔር ይችላል ለሞተው ማንነት ህይወትን ይሰጣል እግዚአብሔር ይችላል ዛሬም ለሚታመን አምላኬ ይችላል እግዚአብሔር ይችላል