እኖራለሁ ባንተ እንቀሳቀሳለሁ በልቼ ጠጥቼ ወጥቼ ገባለሁ ተኝቼ ደግፈኸኝ ከእንቅልፌ ነቃለሁ ደግሞ ባዲስ ምህረት አዲስ ቀን መራለሁ ባንተ ነው መኖሬ መኖሬ ባንተ ነው መኖሬ /2/ ባንተ ነው መሄድ መቀመጤ ባንተ ነው መኖሬ ባንተ ነው መዋሌ ማደሬ ባንተ ነው መኖሬ ባንተ ነው መውጣቴ መግባቴ ባንተ ነው መኖሬ ባንተ ነው መቆም መነሳቴ ባንተ ነው መኖሬ ህይወቴ ህይወትህ ካንተ የተቀበልኩት አለው ልዩ ትርጉም ህይወትህ ህይወቴ ካንተ የተካፈልኩት በዚህ አይለካም የህይወት እስትንፋስ ካንተ አግኝቻለሁ መኖር ደስ እያለኝ እንድኖር ሆኛለሁ የህይወት እስትንፋስ ካንተ አግኝቻለሁ መኖሬን ወድጄው እንድኖር ሆኛለሁ ሰሪዬ ነህ አንተ ፈጣሪዬ መገኛዬ የህይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ ሰሪዬ ኢየሱስ ፈጣሪዬ መገኛዬ የህይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ መሄድ መቀመጤ መቆም መነሳቴ ባንተ እየታዘዘ መላው እኔነቴ ፈጠርከኝ አኖርከኝ እኔ ያንተ መቅደስ አንተም መኖሪያዬ ቤቴም ያንተ ቤት ነው እጅህ አለኝታዬ ፈጠርከኝ አኖርከኝ ሰሪዬ አንተ ነህ ፈጣሪዬ መገኛዬ የህይወት ምንጭ ነህ መኖሪያዬ