Song Lyrics

ምህረትህ ብዙ

Asrat Mulachew
Hiwotih Hiwote
አምላኬ ምህረትህ ብዙ ነው ብዙ ይቅርታህ ብዙ ነው ብዙ ፍቅርህ ብዙ ነው ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ምህረትህ/ ይቅርታህ/ ፍቅርህ/ ትዕግስትህ ብዙ ነው ብዙ ብዙ ነው ምህረትህ/ ይቅርታህ/ ፍቅርህ/ ትዕግስትህ ብዙ ነው እንደበደሌማ እንደ ኃጢያቴ በፈሰሰ ነበር ቁጣህ በህይወቴ እንደ እግዚአብሔር ፍቅር እንደምህረትህ አለሁ እስከዛሬ አልጠፋሁ ከፊትህ አልሆንም እንዳልተደረገለት ሰው አልዋሽም በህይወቴ ባደረገው በብዙ ረድቶኛል ምህረትህ ያኖረኛል ለዘለዓለም በቤትህ በስጋዬ ተመኝቼ ባይኔም አምሮት ተገዝቼ ገሰገስኩኝ ብዙ ርቄ አልቀረልኝም መውደቄ አንተ ግን ፃድቅ ነህ አንተ ግን ይቅር ባይ ፈጥነህ ራራህልኝ ሁኔታዬን ስታይ ደግመህ ተቀበልከኝ አልተፀየፍከኝ በምህረትህ ብዛት ቤትህ ገባሁኝ በምህረትህ ነው ጌታዬ በምህረትህ ነው ቤትህ መግባቴ ጌታዬ በምህረትህ ነው በምህረትህ ነው ጌታዬ በምህረትህ ነው ዛሬን ማየቴ ጌታዬ በምህረትህ ነው አይቻለሁ ምህረቱን ቀምሻለሁ ቸር መሆኑን በየቀኑ ሁሌ አዲስ ነው ፍጥረት ሁሉ ያመስግነው ምህረቱ ትዝ እያለው፣ ባሪያውን ካሰበው፣ ፈቅጄ አመሰግነዋለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection