ቃልህን ላክ ድምፅህን ላክ - የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ መንፈስህን ላክ እጅህን ላክ የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ በሙታን ሸለቆ በመቃብር ላለው ቃልህን ላክ በድካም ደርቆ ከህይወት ለጎደለው ድምፅህን ላክ እስትንፋስን ሰጥተህ ህያው ልታረገው ቃልህን ላክ ከጉድጓድ አውጥተህ ዳግም ልታቆመው ድምፅህን ላክ ቃልህን ላክ ድምፅህን ላክ በመቀባበል የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ ሽባ እንዲተረተር ዕውር እንዲበራ መንፈስህን ላክ ድንቅ ታምራትህ ዛሬም እንዲሰራ እጅህን ላክ ደዌ እንዲፈወስ ቋጠሮ እንዲፈታ መንፈስህን ላክ አምልኮ እንዲቀርብ ለሰራዊት ጌታ እጅህን ላክ ድንበሬን አስፋልኝ ብሎ ለለመነህ መንፈስህን ላክ እጅህን በላዬ ላይ አበርታልኝ ላለ እጅህን ላክ ሊነጋ እስኪያቅላላ ታግሎህ ለጠበቀው እጅህን ላክ በእውነተኛ ባርኮት እንድትገናኘው መንፈስህን ላክ ገበናውን ደብቆ ሊያዋይህ ለመጣ ቃልህን ላክ እንቆቅልሽ ይዞ ፍቺውን ግን ላጣ ድምፅህን ላክ ያንጎዳጉድ ድምፅህ አይከልከል ከሰማይ ቃልህን ላክ ዛሬም እንደጥንቱ ክብርህ በዚህ ይታይ ድምፅህን ላክ