Song Lyrics

ሁሉ መንገድህ

Asrat Mulachew
Amelkihalew
ሃይልህ እጅግ ታላቅ ነው ሁሉንም ይችላል በምድረ በዳ ላይ መናን ይመግባል ምልክት ሳይታይ ዝናብን ይሰጣል ተስፋ ያረጉትን ሁሉ ያሳርፋል በመከራዬ ቀን ቀድሞ ያገኘኝ ከሁሉ ፈጥኖ የደረሰልኝ በወጀብ ባውሎ መሃል መንገድ ያለው እኔ ማመልከው ጌታ እግዚኣብሄር ነው ውሃም የብሱም ሁሉ መንገዱ ነው ምስኪኑን ስታስብ ቁልፉ በእጅህ ነው ማን ይገምተዋል ጌታ አመጣጥህን ከጉድ ታወጣለህ ገልጠህ ማዳንህን ደመናን ሰንጥቆ ቀዶ የሚመጣ ቢያሻው መንገዱ ነው ተራምዶ ሊመጣ እኔን ያስብ እንጂ ምንም ማያግደው እርሱ ከፈለገ ውሃ መንገዱ ነው ማይታለፍ መስሎ የቆመ ተራራ ነጎድጓዱ ቃልህ ሲመጣ እያስፈራ የብረቱን መዝጊያ ያይንህ ጨረር ከፍቶት ቀጥ ባለው መንገድ አለፍን ክብርህ መርቶን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection