አልጥልህም አልተውህም አልረሳህም ብሏል ታዲያ ምን ያሰጋኛል አልጥልህም ጌታ ራሱ አልረሳህም ብሏል ታዲያ ምን ያሰጋኛል ወላጅ አልባ አይደለሁም እኔ በውነተኛ ቃሉ አስቦ ወልዶኛል በምድር ሳለሁ ለጎደለኝ ሁሉ ጌታ ይረዳኛል ሰው ምን ያደርገኛል የወለደኝ ክቡር ህያው ቃሉ ሸላልሞ ቀራርጾ ሁሌ ያሳድገኛል እስከሽበት እስከ ሽምግልና ቤቱ ያኖረኛል ፊቱ ያቆመኛል ወጀብ በዝቶ ልትሰጥም መርከቤ እጅግ ብትናወጥ ብትሰነጣጥቅ ወየሁ ጠፋሁ እያልኩኝ መጮሄ መች ቀልድ ይመሰለዋል የእኔ መጨነቅ ድንገት ደርሶ ያስፈራኘን ማእበል ጸጥ በል ይለዋል ባንዴ ያዘውና በሚያጸና በሚደግፍ እጁ ቀጥ አርጎ ያቆመኛል አትፍራ ይልና