Song Lyrics

መንፈስህን አትውሰድብኝ

Asrat Mulachew
Amelkihalew
• ከፊትህ ጥለህ አትተወኝ እኔስ ያላንተ መግቢያ የለኝ መንፈስህን ከኔ አታንሳብኝ በምድረ በዳም አትተወኝ ሃጢያትን ሰርቼ ስልህ ማረኝ ብበድልህ እንኳን ይቅር በለኝ መንፈስህን ከኔ አታንሳብኝ በምድረ በዳም አትተወኝ አብን አሳየኝ ይህ በቂዬ ነው ጸሎቴም ይኸው ፊትህን ላይ ነው ጌታ አንተን አይቼ ኢየሱስ ልኑር ረክቼ ጌታ አንተን ሰምቼ ልኑር ተረጋግቼ • ዝም ስትለኝ እኔ ይጭንቀኛል ድምጽህ ሲርቀኝ ኑሮ ይከብደኛል ስትናገረኝ እጅግ ረካለሁ ድምጽህን ስሰማው ቶሎ እጽናናለሁ እደሰታለሁ ወዳጄ ስለዚህ ዝም አትበለኝ ለቀሪ ዘመኔ ቃልህን ስጠኝ መኖር ምችለው ተረጋግቼ ድምጽህን ስትልክ አንተን ሰምቼ ካንተ ሰምቼ • ያባቶቼ አምላክ የመራሃቸው እጃቸውን ይዘህ ያሻገርካቸው በታምር ዘለው ክብርህን ቢያስቆጡ ከመንገዳቸው እንደተቀጡ ርስትን እንዳጡ በብዙዎቹ ደስ እንዳላለህ በእልከኝነት እንዳስመረሩህ የኔም ልብ ትቶህ አይሂድብህ ድምጽህን ስሰማ ልታዘዝህ ልኑርልህ • መንገዴ ሳይሆን እንደመንገድህ ሳይሆን ሃሳቤም እንደ ሃሳብህ በጸጋህ ድኜ ባይኖረኝ ጸባይ ክብርህ በህይወቴ እንደምን ይታይ አረ እንዴት ይታይ መንገዴ ሳይሆን እንደመንገድህ ሳይሆን ሃሳቤም እንደ ሃሳብህ በጸጋህ ድኜ ባይኖረኝ ጸባይ ክብርህ በህይወቴ እንደምን ይታይ አረ እንዴት ይታይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection