Song Lyrics

ያላንተ ኑሮ

Asrat Mulachew
Amelkihalew
ያላንተ ደስ ብሎት በምድር ላይ የኖረ ተድላን የቀመሰ የለም የከበር አንተን አጥቶ መኖር አይታሰብም የመኖር ምክንያት ነህ የመኖርም ትርጉም የህይወት ጣእም • መኖሬን ፍቺ ሰጥተኸዋል ህይወቴን መስመር አሲዘሃል በልቤ ገብተህ ስታድርበት ኑሮህን ስትመሰርትበት አማረበት ሰው አንተን ሳያገኝ እንዴት ኑሮውን ይገፋል ዋስትና ሳይኖረው ቆሞ ይንቀሳቀሳል እኔስ ያላንተ ኣንንድ እርምጃ እንኳን አልችልም ላደርግ ብሞክርም ያላንተ አውቃለሁ ትርፉ ሞት ነው • ጭንቅ ነው የሰቆቃ ኑሮ ያላንተ ሁልጊዜ እሮሮ አልችልም እኔስ አልሞክርም ኢየሱስ ከሌለህ በቤቴ እኔ አልኖርም ትናንት ካንተ ጋራ ብዙ አሳልፌ ሞተህ የቀረህ መስሎኝ መንገዴን ታጥፌ ዘመኔን ካንተው ጋር ሀ ብዬ ጀምሬ እንዳልወድቅ ከእጆችህ እንዳልቀር መንገድ ላይ ከሳስሬ በምድራዊው ነገር ስራችንን ሰደን ልትወስደን ስትመጣ መልቀቅ እንዳይከብደን ያላንተ አልበላን ከቶም አላማረብን በኔ ኑሩ እንዳልከን ባንተው ላይ ትከለን አሳድገን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection