• ሰማያት ስፍራቸውን ሳያስቡት በፊት ምድርም መሰረቷን ሳታገኘው በፊት አሶች በውሃ መኖር ሳይጀምሩ በፊት ከሁሉ በፊት ነበርክ በዙፋንህ ሁሉን እየገዛህ ፍጥረት ምስክር ነው ለአምላክነትህ አለህ በዙፋንህ ሁሉን እየገዛህ እኔም ምስክር ነኝ ለአምላክነትህ ክብር በዙፋንህ ላንተ በከፍታ ላለህ ክብር በዙፋንህ ላንተ በሰማያት ላለህ ክብር በዙፋንህ ላንተ ከጥንት ለነበርህ ክብር በዙፋንህ ላንተ ሁሉን ለፈጠርህ • ውቅያኖስ ጠብታን ከማግኘቱ በፊት ከዋክብት በሰማይ ሳይታዩ በፊት ምድረም ሳር ቅጠሏን ከማብቀሏ በፊት ከሁሉ በፊት • ጨለማው በጥልቁ ከመሆኑ በፊት እለታት አመታት ሳይለዩ በፊት ወፎች ከምድር በላይ ሳይታዩ በፊት ከሁሉ በፊት • ምድር ፍጥረታትን ከማውጣቷ በፊት ሰው ባንተ ተፈጥሮ ከመግዛቱ በፊት ካማልክት ካለቆች ከስልጣናት በፊት ከሁሉ በፊት