Song Lyrics

ደስ ይለኛል

Asrat Mulachew
Amelkihalew
ወደ ደጆቹ በመገዛት እገባለሁ ባደባባዩ በምስጋና እታያለሁ ወደ መቅደሱ በአምልኮ እዘልቃለሁ ስሙን ሳነሳ ሳወድሰው መች ጠግባለሁ በእውነተኛ ቃሉ አስቦ የወለደኝ የድካሙ ፍሬ የደሙም ዋጋ ነኝ በለመለመ መስክ ሁሌ የሚያሰማራኝ ገና ከፍጥረትም የእጆቹ ስራ ነኝ ነፍሴ ሃጢያቷ ተነስቶላት ደስ ብሏታል የክስ መዝገቧ ተገልብጦ ደስ ብሏታል መካከለኛው ከመሃል ገብተህ ደስ ብሏታል የጥል ግድግዳን በደምህ አፍርሰህ ደስ ብሏታል ባንተ ደስ ይለኛል ሃሴት አድርጋለሁ ምንም በእጄ ባይኖር ባንተ እደሰታለሁ ከወይን ጥጅ ይልቅ ፍቅርህን አስባለሁ ሁሉም ቢሞላልኝ ተመስገን እላለሁ መች ጠግባለሁ ሳወድሰው እኖራለሁ ደስ ደስ እያለኝ እግዚኣብሄርን አመልካለሁ ደስ ደስ እያለኝ ለልኡሉ እገዛለሁ በብዙ ደስታ ወደፊቱ እገባለሁ ሁሌ ሳመልከው ሳስደስተው እኖራለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection