በሰማይ በምድር ትልቅ እግዚኣብሄር ትልቅ ኢየሱስ ነው ትልቅ መንፈስ ቅዱስ ትልቅ ቀን ለቀን ስራህን አብዝቶ ቢያወራ በማይሰማ ድምጽ ክብርህን ቢያደራ ሌሊት ለሌሊት ቢገልጥ እውነትህን ሚታይ ማይታየውን ድንቁን ጥበብህን ታላቁን ስራህን ሰምቼ ነፍስም አልቀረልኝ ዛሬ አይቼ ከእጆችህ ስራ ስትበልጥብኝ ትልቅ አንተ ብቻ ነህ አልኩኝ ትናንትና አልፎ አዲስ ቀን ሲመጣ ስልጣን ተሽሮ በስልጣን ሲተካ ሺህ አመት ንገስ ብለው ሰይመው መገባደጃው ደርሱ ፍጻሜው ይገርማል ሲሻር ሲነሳ ግዛቱ አክትሞ ሲረሳ የዘላለም ሆነህ ብናይህ ግዛን አንተ ብቻ አልንህ የህዝብን ለቅሶ ጩኸትና ዋይታ እንቆቅልሹን ጠፍቶ የሚፈታ መጽሃፉን ልትከፍት ማህተሙን ልትፈታ እንደቻልክ ሳውቀው መሆንህን ጌታ መጽሃፉን ወስደህ ስትከፍተው ሃጢያቴን ስትደመስሰው ከቅዱሳን ያኔ ስትበልጥብኝ ቅዱስ አንተ ብቻ ነህ አልኩኝ ክቡር ሆነህ ሳለህ ከላይ መውረድህ ኤፍታህ ልትለን መንቀሳቀስህ የባርያን መልክ ስትይዝ ጌትነትክን ጥለህ ልጆቼ ስትለን ካለንበት ደርሰህ እስከመጨረሻ ወደኸን ላትጥለን በደምህ ገዝተኸን በዚያው ፍቅርህ ዛሬም ብናይህ ፍቅር አንተ ብቻ ነህ አልንህ