እግዚኣብሄር አለቴ አምባ መድሃኒቴ እወድሃለሁኝ አንተ ነህ ጉልበቴ በቀናው መንገድህ ሁሌ እየመራኸኝ እንዳልንሸራተት መሰረት የሆንከኝ • ለመንገዴ ብርሃን ለእግሬ መብራት ሆነህ ቀናልኝ ጉዞዬ ከፊት ፊቴ ሂደህ መሪዬን ይዘኸው ቀድመህ እየሳብከኝ ምስጋና ይብዛልህ እዚህ አደረስከኝ ተራራ ሸለቆውን ወጥቼ ብወርድም ከኔው ጋር መሆንክን ባልገነዘብም ጨለማዬን አይተህ ይብራ እያልከኝ ብርሃኔ ሆነህ ነው የዛሬ የሆንኩኝ • ብርሃኔና መድሃኒቴ እግዚኣብሄር ነው ሌባው እንዳይገለኝ ከቶ እንዳያገኘኝ ህይወትን አብዝተህ አብዝተህ ሰጠኸኝ ድምጽህን እያሰማህ እያስከተልከኝ ለካስ መርተኸኝ ነው መንገድ ያልሳትኩኝ • ብርሃኔና መድሃኒቴ እግዚኣብሄር ነው የድንገት አይደለም ያጋጣሚ ነገር ተወልዶ ማደጌ የመኖሬ ትርጉም አላማህ በኔ ላይ ጽኑ ሆኖ ከጥንቱ በፍቅርህ መያዜ ከስር መሰረቱ • ብርሃኔና መድሃኒቴ እግዚኣብሄር ነው ጨለማ ባንተ ዘንድ አይጨልምምና ሌሊቱም እንደቀን ያበራልና ብርሃኔ ነህ አንተ ብርሃን ያየሁብህ ከጨለማው አለም ያመለጥኩብህ