Song Lyrics

እረፍቴ አንተ ነህ!

Asrat Mulachew
Amelkihalew
እርፍ አለች ነፍሴ እርፍ አለች ነፍሴ ስላያዘች አንተን በህይወት ስላኖርካት ሰብረኸው ቀንበርዋን አድሜን አስቆጠሮ ከከበዳት በላይ የተሰቀልከውን ቀና ብላ ስታይ መጣሁ ካለሁበት ዝናህን ሰምቼ ነፍስም አልቀረልኝ ክብርህን አይቼ ከሰማሁት በላይ ሆንክልኝ ከሰለሞንም በለጥክብኝ እርፍ አደረከኝ አንተው ክበርልኝ እርፍ አለች ነፍሴ እርፍ አለች ነፍሴ ስትባርክህ አንተን ሁሌ እያስታወሰች ደግነት ምረትክን እንዳትቅበዘበዝ ደግማ እንዳትጉላላ ወስደህ አስቀመጥካት በክብር ሰረገላ እረፍቴ አንተ ነህ እርፍ አለች ነፍሴ እርፍ አለች ነፍሴ ኣይኗ ሲበራላት ካንተ በመኖሯ ብዙ ረፍት ሆኖላት አያልፉትን ሁሉ አንተ እያሳለፍካት ብቻህን ተናጥቀህ ካጥፊው እጅ አዳንካት እረፍቴ አንተ ነህ እርፍ አለች ነፍሴ እርፍ አለች ነፍሴ አንተ አሳርፈሃት ሞቷን ሞተህላት ከሞት ሰላዳንካት አንድም ላያገኛት ትናንት የፈራችው ዳግም ላታያቸው ስላሰመጥካቸው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection