Song Lyrics

አንተ ነህ አባቴኝ

Asfaw Melese
Tilant Zare Ayidelem
ሰው እንዳለህ አይደለህም አእምሮ እንዳሰበህ ከመጣው ሁሉ ታልፋለህ ከተነገረልህ (2x) ከሚሉህ በላይ ነህ ጌታ ከሚሉህ በላይ ከሚሉህ በላይ ነህ አምላኬ ከሚሉህ በላይ (2x) ብዙዎች አውቀናል እንዳሉ በራሳቸው አእምሮ እንዳሰሉ አንተ ግን እንደዛ አይደለህም ትልቅ ነህ ማንም አያውቅህም አስገረመኝና ሥራህ ማልጄ ተነሳሁ ላመልክህ ፈቃዴን ሰጠሁ እራሴን ግዛኝ ኢየሱሴ ግዛኝ ኢየሱሴ (8x) አላፋው አግዳሚው እንዳለህ አውቀናል ብለው እንዳወሩ ሺህ ቃል ቢደረደር አይገልፅህ አምላኬ ከመባል ታልፋለህ በትላንቱ ነገር ስገረም ዛሬም አስደነቅከኝ ዳግም ተዓምራትህ በዛ በሕይወቴ አንተ ነህ አባቴ አንተ ነህ አባቴ (10x) እስከመቼ ያልኩኝ ፍቺ ላጣው ህልሜ ምላሽን ሰጥቶኛል እንዳልቀር ደክሜ ጌታ ባየኝ ወራት እንዲህ ሆኖልኛል አንደበቴም ሁሉ ዛሬማ ምሥጋናን ያወራል ዘመርኩበት ባለቀስኩበት ዘመርኩበት አይሆንም ባልኩበት ዘመርኩበት ባጉረመረምኩበት ዘመርኩበት በጠላቶቼ ፊት (3x) ምንም ታናሽ ቢሆን ጅማሬው የተነሳበት ፍፃሜው ትልቅ ነው በአምላኩ የሚደርስበት እጅህን አታንሳ በድፍረት ጌታ በገባው ላይ ስለ እርሱ ተዋጊ ተሟጋች አለና በሰማይ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection