Song Lyrics

ከፍታዬን ልያዝኝ

Asfaw Melese
Tilant Zare Ayidelem
የጠላቶች ቁጣ ቢነድም በላዪ ከእነርሱ ይበልጣል አዎ የጠራኝ ጌታዬ ልቤም አይደነግጥ በወጀቡ ብዛት መንገድ ላይ አይጥለኝም ጌታ እኔ የታመንኩበት (2x) ወጀቡን አይቼ ፀጋዬን አልጥልም የከበረውን ነገር አዎ ለውሾች አልሰጥም እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ጉልበቴ አይላላም በጠላቴ ዛቻ እኔ ስፍራዬን አለቅም (2x) ከፍታዬን ልያዝ ተራራውን እግዚአብሔር ለእኔ ያየልኝን አልደከምኩም ዛሬ ጉልበታም ነኝ የሰማሁት ወንጌል አላረጀም (2x) ዮርዳኖስን አይተው እህ ሰዎች ብዙ ቢሉ እኔ እሻገራለሁ ሰምቻለሁ ቃሉን አዬ ሰምቻለው ቃሉን ካየልኝ በረከት እህ ከግቤ ላይ ሳልደርስ ኦሆ ወጀቡን አይቼ እኔስ አልመለስም አዬ እኔስ አልመለስም እልፍ በል ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው መንገዴን ጀምሬ እንዴት እመለሳለሁ ከእኔ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል ልቤም ላይደነግጥ ይህን ቃል አምኖታል ኧረ እንዴት ይሆናል ብዬ እህ ብዬ አልጠራጠር ኦሆ እግዚአብሔር ከሰጠኝ ተራራማውን አገር አዬ ተራራማውን አገር ፈርቼ አልመለስም እህ ረጃጅሞቹን ኦሆ እገጥማቸዋልሁ ጠርቼው አምላኬን አሄ ጠርቼው አምላኬን እልፍ በል ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው መንገዴን ጀምሬ እንዴት እመለሳለሁ ከእኔ ጋራ ያለው ከሁሉ ይበልጣል ልቤም ላይደነግጥ ይህን ቃል አምኖታል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection