መሰዊያዬን ልስራ ከማጠኔ በፊት ከድንኳኔ ላውጣ አንተ የማትከብርበትን አዎ እንጨቴን ልረብርብ አንድደው እሳቴን መስዕዋት አድርጌ ላስቀምጠው እራሴን (2x) አንተን ደስ ካለህ አምልኮዬ አንተን ካከበረህ ኑሮዬ ክበርልኝ ጌታዬ (2x) ክበርበት ጌታዬ (2x) የመኖሬ ሚስጥር የመክበሬ ጅምር አንተ አይደለህም ዎይ እግዚአብሔር (4x) የእኔ ከፍታዬ አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (2x) የእኔ የብቻዬ አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (2x) መከበሪያዬ አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (2x) የእኔ ማረፊያዬ አንተ አይደለህም ዎይ ጌታዬ (2x) ሰማይን በስንዝር የለካህ ምድርንም በቃልህ ያፀናህ እግዚአብሔር አንተ ትልቅ ነህ (4x) አላክብር አላምልክ የልቤ ጌታ ነህ አላርክ አላነግሥ የቤቴ ጌታ ነህ ላይ በሰማይ በዙፋንህ ሆነህ በምድር ያለውን ሁሉን ትገዛለህ የሚሳንህ የለም ሁሉን ትችላለህ እግዚአብሔር ትልቅ ነህ (2x)