Song Lyrics

ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁኝ

Asfaw Melese
Tilant Zare Ayidelem
በምንም አልሰጋም ልቤም አይደነግጥ በሆነው ባልሆነው ምንድን ነው መናወጥ ስለ ነገ እያሰብኩ እኔ አልጨነቅም እግዚአብሔር ሳያውቀው በእኔ የሚሆን የለም አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ ሸክሜም ይኸው በፊትህ ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ (2x) ለማይሞልውና ለዚህ ዓለም ነገር ታዲያ ለምንድን ነው መጨነቅ መሸበር ትላንት ዛሬ አይደል ይህንን አውቃለሁ ጠላት ይስማው እንጂ ድሌን ዘምራለሁ አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ ሸክሜም ይኸው በፊትህ ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ ምክኒያቱ ጌታ ነው ዛሬን ለመኖሬ ስንቱን በእርሱ አልፌ ስንቱን ተሻግሬ እግዚአብሔር ስላለኝ ነገንም ደፍራለሁ ዘመኑን ዋጅቼ በቀኑ ኖራለሁ አዝ፦ እኔማ ሀሳቤን በአንተ ጥያለሁ ሀዘኔን በአንተ ጥያለሁ ሸክሜም ይኸው በፊትህ ናፍቆቴ መኖር በእረፍትህ ነፍሴ አትማረሪ አታስጨንቂኝ እግዚአብሔር ያለው ነው የሚሆንልኝ በሰው አልታመን እኮ ሥጋ ለባሹን ጌታ ይሰጠኛል መከናወኔን እ ነፍሴ አትማረሪ እ አታስጨንቂኝ እ እግዚአብሔር ያለው ነው ተዪኝ የሚሆንልኝ እ በሰው አልታመንኩ እ ሥጋ ለባሹን እ ጌታ ይሰጠኛል ተዪኝ መከናወኔን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection