Song Lyrics

ትዝ ይለኛልኝ

Asfaw Melese
Tilant Zare Ayidelem
ትላንትን ሳስበው በዛሬ ላይ ሆኜ ስንቱን አልፊያለሁ እኔ አንተን መክሬ (2x) ምንድን ነው ስል እንደዚህ ያቆመኝ ምህረትህ ነው ለእኔ ትዝ የሚለኝ አባት መሆንህ ነው ለእኔ ትዝ የሚለኝ አዝ፦ ትዝ ይለኛል ስለ እኔ ያነባ በመስቀል ላይ የጣለ ትዝ ይለኛል አንተ ሞትህ ለእኔ እኔን ልታኖር ትዝ ይለኛል መነሻ ሳይኖረኝ እንዲህ የወደድከኝ ትዝ ይለኛል በፍቅርህ እኮ ነው ኧረ እኔን ያስጣለኝ (2x) ለካስ ልክ ነበር ስትነግረኝም ያኔ ዛሬ ደርሼበት አይቻለሁ በዓይኔ (2x) አላማርርህም ሳስብ መፈጠሬን ለእኔ ተስማምቶኛል ከአንተ ጋር መኖሬ (2x) አዝ፦ ትዝ ይለኛል ስለ እኔ ያነባ በመስቀል ላይ የጣለ ትዝ ይለኛል አንተ ሞትህ ለእኔ እኔን ልታኖር ትዝ ይለኛል መነሻ ሳይኖረኝ እንዲህ የወደድከኝ ትዝ ይለኛል በፍቅርህ እኮ ነው ኧረ እኔን ያስጣለኝ ትዝ ይለኛል ርህሩሁን አብርደህ በረድ ስታኖረኝ ትዝ ይለኛል እንደ አባት ሆነህ መክረህ ያሳደከኝ ትዝ ይለኛል ያንን ምድረበዳ በአንተ ያለፍኩበት ትዝ ይለኛል በሕይወት ያኖረኝ የምህረትህ ብዛት ነፋሱም ሳይነፍስ አይኖርም ደመና በስብከት ሞኝነት ተቀበልኩህና (2x) ስለ አንተ ሲወራ ከሩቁ ሰምቼ ቀርቤ አየሁኝ ማዳንን በዓይኖቼ አባት መሆንህን አየሁኝ በዓይኖቼ አዝ፦ ትዝ ይለኛል ሐሩሩ አብርደህ በረድ ስታኖረኝ ትዝ ይለኛል እንደ አባት ሆነህ መክረህ ያሳደከኝ ትዝ ይለኛል ያንን ምድረበዳ በአንተ ያለፍኩበት ትዝ ይለኛል በሕይወት ያኖረኝ የምህረትህ ብዛት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection