አዝ፦ ትላንት ተብሎ ዛሬ ሊጠራ አሳልፎት ነው እግዚአብሔር ሁሉን በተራ አምላኬን እንዲህ በሉልኝ ሥራህ ግሩም ነው እርሱ በሰራልኝ ተዓምራት/ቀናቶች እኔ ኖራለሁ (2x) ልዩነት አምጥቶ ሌሊቱ ለጠላቴ ሆነ ውድቀቱ ሊያጠፋኝ ነበረ ምኞቱ እንዲሁ ደከመ በከንቱ እኔማ አምልጫለሁ ወጥመዴ ተሰብሮ ጠላቴ ላይደግም አንድ ጊዜ ጥሎ እኔማ አምልጫለሁ ወጥመዴ ተሰብሮ ጠላቴ ላይደግም ከእግሬ በታች ጥሎ ይጨምራል ገና ሙሉ ቀን እስኪሆን (2x) የአምላኬን ተዓምራት አያለሁ ማዳኑን (2x) ለነገም ለዛሬ ምላሽ አለው ጌታ በጭራሽ አልወርድም እኔ ከአየልኝ ከፍታ አዝ፦ ትላንት ተብሎ ዛሬ ሊጠራ አሳልፎት ነው እግዚአብሔር ሁሉን በተራ አምላኬን እንዲህ በሉልኝ ሥራህ ግሩም ነው እርሱ በሰራልኝ ተዓምራት/ቀናቶች እኔ ኖራለሁ (3x) ደሙ በመቃኔ በጉበኔ ላይ ነው (2x) ቀኑ ክፉ ቢሆን ነግሬው አልፋለሁ (2x) በሞት ጥላ ብሄድ መቼ ያስፈራኛል ሰባሪው እግዚአብሔር ከፊቴ ቀድሞ ወጥቶልኛል (2x)