Song Lyrics

እንደ እግዚአብሔር ያለ

አዝ፦ አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ የልቤን ተረድቶ እንባ የሚያብስ ከዓይኔ (2x) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (3x) ትናንትና እንዴት ይታለፍ ጭንቅ ነበር ለብቻ ሲታሰብ በዙሪያዬ ጠላት ከቦኝ ማን ያድነኝ ብዬ ተረበሽኩኝ ሰማያት ተከፈቱና በተከበበው ከተማ ምህረቱን አበዛልኛ (2x) ዛሬም ከእኔ ጋራ ነህ (6x) አዝ፦ አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ የልቤን ተረድቶ እንባ የሚያብስ ከዓይኔ (2x) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም (3x) ስደክምበት ዞር በይ ደካማ አላለኝ ደግ ነው ጌታ አቅም ሆነ ኃይል አስታጠቀኝ በከፍታ ላይ አቆመኝ ሰማያት ተከፈቱና በተከበበው ከተማ ምህረቱን አበዛልኛ (2x) ዛሬም ከእኔ ጋራ ነህ (6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection