ጠላቴ ብዙ ብዙ ይጮሃል ጆሮም አልሰጠው ይደክማል ለእኔ የሆነልኝ እንደዚህ ነው የዜማ ጊዜ ደርሶ ወይን አብቦልኝ ነው (2x) በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል ጌታውን የጠበቀ ይከብራል ከአምላኩን ተማምኖ የከሰረ የታል በጊዜው ሰዓቱ ሁሉ አምሮለታል (2x) ማልጄ ልነሳ ከበሮዬን ላንሣ አምላኬን ላመስግን ላሰማ የድል ዜማ አስጨናቂው ለሊት አልፎልኛል ኢየሱስ ብርሃኔ በርቶልኛል (2x) ውሎ የማድር ብሆን ከንጉሥ ደጅ አፍ ክፉ የሚታሰበ ከንጉሥ ወዳጅ ጌታውን ለጠበቀ ነገሩ ተገለበጠ በክፉው ምክር ላይ እግዚአብሔር ተገለጠ (2x) ማልጄ ልነሳ ከበሮዬን ላንሣ አምላኬን ላመስግን ላሰማ የድል ዜማ አስጨናቂው ለሊት አልፎልኛል ኢየሱስ ብርሃኔ በርቶልኛል (2x)