በጊዜያዊው ነገር ልቤ እንዳይሸነፍ በሚያልፈው ነገር ነፍሴ እንዳትታለፍ ቃልህን በልቤ ሰውረው ጌታዬ ትዛዝህን ልጠብቅ ማስተዋል ይሁነኝ ወዳጄ ጥበብህ ትሁነኝ እህቴ (2x) ያንተውማ ነገር ለምን ይይዘኛል የሚያልፈው ነገር ለምን ያታልለኛል ከንቱውማ ነገር ለምን ይይዘኛል የሚያልፈው ነገር ለምን ያታልለኛል ለምን ለምን አሄሄ (2x) ትላንትና የናቁትን ከንቱ ብዬ ያጥላላሁትን ዛሬ ደግሞ ልወዳጀው ለምንድን ነው እንዲህ ፍቅር/ጓደኛ እምሆን (2x) ባሞግስህ ደግሞ መልሶ ሲያሟግ ባከበርህ ደግሞ ሲያማርርብኝ ክፉ ደጉን ሁሉ እየተናገረ ይሄ አንደበቴ አንተን አስመረረ በአንደበቴ ላክብርህ ደስ የሚልህን ልናገርልህ (2x) ያምራል ስባል ሞት ነው ብዬ ትናንትናን ንቄው ዘግቼው አልፌ ዛሬ ደግሞ ምን ተገኝቶ የናቁትን ማየት ኋላ ተመልሶ በአደባባይ ላይ ቆሜ ላመልክህ ከቅዱሳን ጋራ ሆኜ በፊትህ ያልሆንኩትን ሆኜ በሰው ፊት ስታይ መጥፊያዬ እንዳይሆን የምልህ አለኝ በጓዳዬ ሆኜ ላክብርህ ሰው ያላየው ባህሪዬ ያስደስትህ በጓዳዬ ሆኜ ላክብርህ ድብቅ ገመናዬ ያስደስትህ እኔ በቃኝ (2x) መሸነፍ በቃኝ እኔ በቃኝ (2x) መታለል በቃኝ አዎ በቃኝ (2x) መታለል በቃኝ አዎ በቃኝ (2x) መሸነፍ በቃኝ በቃ በል እስቲ ጣልቃ ግባና ሁሉ የሚያምረው በአንተ ነውና በቃሽ በለኝ ጣልቃ ግባና ሁሉ የሚሳካው በአንተ ነውና