እኔን ለክብር ለሽልማት ያበቃኝ እግዚአብሔር ከትቢያ ላይ አነሳኝ (2x) በሰው ዓይንም አልሞላ ነኝ እኮ ደካማ ግን እኔ ማን ነኝ የተወደድኩኝ በእግዚአብሔር የተመረጥኩኝ (2x) ከሰው ተራ የሚያድን መልካም ነገር የለኝ ጐሽ የእኔ ልጅ ተብሎ የሚያስመሰግን ምህረትህና ፍቅርህ ሰው አድርገውኛል ከቅዱሳን ጋራ ያዘምሩኛል አዝ፦ ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (2x) እርቃንህን አደባባይ እንደ ወንጀለኛ ምንም ሳታጠፋ ስለ እኔ ተገፋህ ያ ሁሉ ልፋትህ እኔን ለማዳን ነው ከክብርህ ወርደህ ዝቅ ዝቅ ያልከው አዝ፦ ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (2x) እኔን ለክብር ለሽልማት ያበቃኝ እግዚአብሔር ከትቢያ ላይ አነሳኝ (2x) በሰው ዓይንም አልሞላ ነኝ እኮ ደካማ ግን እኔ ማን ነኝ የተወደድኩኝ በእግዚአብሔር የተመረጥኩኝ (2x) ሰው ሰውን የሚወደው በእራሱ ምርጫ ነው ድካም ያለበትን ማነው የሚቀበለው አንተ ግን ስትወደኝ ስትቀበለኝ ደካማ ነሽ ብለህ ፊትህን አልነሳኸኝ አዝ፦ ተሰጥቼ ፊትህ ሆኜ እኔ ባመልክህ ያንስብሃል ለውለታህ ሲታሰብ (2x)