አዝ፦ በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት (2x) ከእኔ ነው የምለው ምንም ነገር የለም ለመዳኔ ምክኒያት ምንም አልፈጠርኩ ታሪኬ እንዲያምር ከክብሩ ወረደ ሕይወቱን ሊሰጠን እራሱን አዋረደ ወዶኛልና አዳነኝ (4x) አዝ፦ በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት ሰራሁት የምለው አከናወንኩት ዛሬ ለመድረሴ እኔስ ለፋሁበት የምለው የለኝ ድካሜ ነው ቀላ ግን በእርሱ ምህረት እዚህ ደርሻለሁ ወዶኛልና አዳነኝ (4x) አዝ፦ በኃይሌ እንዳልል ሰው አይበረታ በኃይሉ አቅሜ እንዳልል የለኝም ጉልበት እኔን ለማዳን ነው ስቃዩ የበዛው የደም ላብ ያላበው በመስቀል የሞተው ሞቴን የሞተልኝ ነጻ አውጥቶኛል የዘለዓለም መንግሥት ወራሽ አድርጐኛል ወዶኛልና አዳነኝ (4x)