የሚገርመኝ እኔ ቅጥሩ ታላቅ ነው ማንም እንዳይነካኝ ለእኔ ያሰበው ተዘልለሽ ኑሪ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ ለምን ትፈሪያለሽ . (1) . አዝ፦ እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ተነሳሁ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ ሰላም ኑሪ አለኝ (2x) እኔን የሚጠብቅ አይተኛ አያንቀላፋ ይልቁን በእሳቱ ጠላቴን አጠፋ ክንዱ ተዘርግታ አርፌ በጌታ ሳልሰጋ ኖራለሁ ሁልጊዜም በደስታ እርግማን እንዳይሰራ በዘመኔ ሟርትም እንዳይሰራ በዘመኔ ቅጥር ሆንከኝ መድህኔ (3x) አዝ፦ እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ተነሳሁ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ ሰላም ኑሪ አለኝ (2x) የጠላቴን ምክር ዛቻውን እንዳልፈራ በእሳት የሚመልስ አለኝ የሚያኮራ ዙሪያዬ ቢዞር ጠላት ቢጮህ መናወጥ አላውቅ ሰላሜ አይጠፋ እግዚአብሔር ብሎኛል ልጄ እረፊ በዘመንሽ ሁሉ ሰላም ለአንቺ ሰላም ይሁን ከቤትሽ (3x) አዝ፦ እግዚአብሔር ሲናገር ሰማሁ ተነሳሁ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ ሰላም ኑሪ አለኝ (2x)