ይመጣል ኢየሱስ ኢየሱስ ይመጣል በታላቅ ብርሃን ተገልጦ መልአኩ አዋጅ ነገራቸው ለእረኞች ሁሉ ንጉሥ ተወለደ በቤተልሔም ከተማ ሄዳችሁ ስገዱ በግርግም አለና (2x) መላዕክት ያወጁለት እረኞች የሰገዱለት አዝ፦ ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን (2x) ላሰናዳው ቤቴን ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (2x) ላሰናዳው ቤቴን ኢየሱስ ይመጣል ኢየሱስ ይመጣል በቃላ ገሊላ ጀመረ ተዓምሩ የአባቱን ፈቃድ ፈፀመ ትዕዛዙን ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት በመስቀል የሞተው ኢየሱስ ይመጣል ቤቴን ላሰናዳው አዝ፦ ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን ላሰናዳው ቤቴን ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (2x) እኔስ ልሁን ከልባሞቹ መቅረዜን ልሙላ አላንቀላፋ ድንገት ሲመጣ ይኼ ወዳጄ እንዳልቀር ኋላ ካሁኑ ልንቃ አዝ፦ ይሄ ወዳጄ ድንገት ይመጣል እንዳልቀር ከደጅ ላሰናዳው ቤቴን ላሰናዳው ቤቴን ንፁህ ላድረገው ሕይወቴን (2x) የምድሩ ክብር ዝናው ሲደምቅልኝ አቤት ጭብጨባው ሞቅ ብሎ እንዳልዘነጋ ተይ ነፍሴ ሙግትሽህ ምንድን ነው አይግረምሽ አይድነቅሽ መዝገብም አይሆን ለላይኛው ቤቴ ተይ ተይኝ ነፍሴ ተይኝ ከአምላክሽ ጋራ ተስማሚልኝ የሚረባን የሚያውቅ እርሱ አይደለም ዎይ የሚበጅሽንስ እርሱ አይደለም ዎይ በቃ ተይኛ ነፍሴ ተይኝ ከአምላክሽ ጋራ ተስማሚልኝ