የሕይወት መገኛ የዘለዓለም ውረት ፈቃድህን ማድረግ ለሀሳብህ መወገድ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ ያኔ የልጅህን መልክ እንድንሰው ነው ውሳኔ ከታናሽነቴ ከብላቴንነት የመረጥከኝ ጌታ በቤትህ እንድኖር የለየኸኝ ጌታ በጐና ደስ የሚያሰኝ ፍፁም የሆነው ፈቃድህ ይፈፀም ዘንድ በሕይወቴ ጣልቃ ግባ በእያንዳንዱ ነገሬ የሚረባኝ የሚበጀኝን ታውቅልኝ አይደል አባቴ (2x) ፈቃድህ ይፈፀም በሕይወቴ (3x) አላማህ ይፈፀም በሕይወቴ (3x) ለእኔ ብዬ የምተወው (የምተወው) አንድም ነገር የለም የምሸሽገው ሁሉን ለአንተ ሰጥቻለሁ (ሰጥቻለሁ) ፈቃድህ እንዲፈፀም እወዳለሁ ችላለሁ ብዬ የምተወው አንድም ነገር የለም የምሸሽገው ሁሉን ለአንተ (ሁሉን ለአንተ) ሰጥቻለሁ ፈቃድህ እንዲፈፀም እወዳለሁ የአንተ ሀሳብ የአንተ አላማ የአንተው ፈቃድ በዘመኔ ይፈፀም (2x)