Song Lyrics

እርስቴ ነህ

አንተ ላወቁብህ ክብር ነህ የማዕረግ መጐናፀፊያ የሃዘኑ ዘመን ማስረሻ ከማይነጥፍ ሰላም መድረሻ በዕረፍት ወንዝ ዳር ይተከላል ያገኘህ ከምንጭ ዳር ይኖራል ዕርዳታው ከሰማይ ደጅ ይወርዳል የእግዚአብሔር/የአምላኩ እጅ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x) በሰማይ በምድር ማይገኝ ቢተካስ በሌላ ማያሰኝ መኖሪያህ በብርሃናት ውስጥ ውበት ነህ ለርስትህ ጌጥ ለዘለዓለም ትኖራለህ ማያረጁ ዓመታት ይዘህ ለሁሌ ነህ የነፍሴ/የእኔ ምርጫ ከአዕላፋት አግኝተህ ብልጫ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x) ለሰማይ ዉበትን የሰጠህ ለምድር ዳርቻን ያበጀህ እኔን በአምሳልህ መፍጠርህ የከበርሁ አርገህ ማየትህ ልቤ በመደነቅ ተሞላ ክብሬ ሊያዜምልህ ተነሳ ከልብ የሚፈልቅ ምሥጋና መስዋዕቴ ወደ ላይ ይግባ (2x) አዝ፦ እርስቴ ነህ የልቤ ምርጫ ነፍሴ አፀደቀህ የፈቃዴ ብልጫ ሁሉንም ንቄያለሁ ክብር በፊቴ አጣ ሁሉን ጥሎ ነፍሴ ወደ ሃሳብህ መጣ ጌታ ፍቅርህ እጅግ እያየለ መጣ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection