ከቶውን በለስ ባያፍራ ከወይንም ሃረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ የወይራ ሥራ ቢጐድል እርሾችም መብልን ባይሰጡ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያበረታ በከፍታዎች ላይ ያስኬደኛል (2x) አምላኬ ደስታዬ ደስታዬ ነህ ኢየሱሴ ሙላቴ እርካታዬ ነህ (2x) በቅተኽኛል ሌላም አልፈልግም ቀረም የምለው ነገርም የለኝ ታምኜብህ በሁሉ ነገሬ ይዤ መጣሁ የከንፈሬን ፍሬ (2x) ምን ይከብደው ብዬ ለየትኛው ልፍራ/ልስጋ ምን ያቅተውና ምኑን ብዬ ልፍራ (2x) ተራራ ላይ ማዳን የቻለው ሸለቆው ውስጥ ኃይል የእርሱ ነው ሁሉን የሚችል ሥሙ ኤልሻዳይ የእኔ አምላክ ያለ በሰማይ (2x) እንደ እግዚአብሔር ያለ ከወዴት ይገኛል የሕዝቡ መከታ ፅኑ ጋሻ ሆኗል (2x) መመኪያ ነው ለትውልድ ትምክህት መጓደጃ የልጅ ልጅ ኩራት ሚታመኑት ከፍ ከፍ ይላሉ ለዘለዓለም ማዳኑን ያያሉ ከቶውን በለስ ባያፍራ ከወይንም ሃረግ ላይ ፍሬ ባይገኝ የወይራ ሥራ ቢጐድል እርሾችም መብልን ባይሰጡ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለእኛል በመድኃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያበረታ በፍታዎች ላይ ያስኬደኛል (2x)